አዲስ ዘመን መጋቢት 13/2018
Apr 06, 2026
11
Addis Ababa
100 ETB
3,000,000.00
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 014/2018
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የማተሚያ ማሽኖች ግዥ ከቅድመ ህትመት እስከ ድህረ ህትመት (sheet fed offset press, folding machine, paper cutting machine, perfect binding machine, double saddle stitcher, laminating machine, heavy duty printer, thermal ctp) በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት በውል ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስስሆነም:- ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
* በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
* የንግድ ምዝገባ
* የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት
የቫት ሰርተፍኬት
* በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበ
* የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3,000,000.00(ሶስት ሚሊዮን ብር)በሲ.ፒ.ኦ፣ቢድ ቦንድ ወይም ለጥቃቅንና አነስተኛ ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ በማያያዝ ይህ ጨረታ አየርላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት አንደኛ ፎቅ በሚገኘው አቅርቦት መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል ዶክመንት ዋና እና ቅጂ እንዲሁም የሚወዳደሩበትን ዋጋ ዋና እና ቅጂ በሚል በጉልህ በሚታይ መልኩ በመጻፍና የሚወዳደሩበትን ሎት በፖስታዎቹ ላይ በመግለጽ በአራት የተለያየ ፖስታ በማሸግ በአንድ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
* በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
ስርዝ ድልዝ ያለውና ያልተፈረመ እንዲሁም በጉልህ የማይታይ አጠራጣሪ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
* ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ 1ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን የተጫራቹ አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም፡፡የጨረታ መክፈቻው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
ድርጅታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡-አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት