አዲስ ዘመን መስከረም 14፣2018
Oct 06, 2025
16
Addis Ababa
500 ETB
50,000
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 12
የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን በስሩ ያሉትን ለተለያዩ ፓርኮች ማለትም
ሎት 1- የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳዳር ኮርፖሬሽ በውስጡ የሚያስተዳድራቸው በኮርደርልማት የለሙ በአቃቂ ኮዬ፣ መገናኛ፣ ሽሮ ሜዳ አካባቢ፣ ግንፍሌ፣ ሳር ቤት፣ ለቡ፣ ጀሞ፣ መካኒሳ፣ ኦሮሚያ ኮንዶሚንየም፣ ቡልቡላ፣ ለሚኩራ ፣ ሰሚት፣ አቦ አካባቢ፣ እንጦጦ ፓርክ ውስጥ፣ ጎሮ፣ ኮሪያ ፓርክ ውስጥ፣ ልደታ፣ ገርጂ መብራት ሀይል አካባቢ፣ ገርጅ ኦቪድ ሪል ስቴት
አካባቢ ቡልቡላ መንገድ፣ስብሰባ ማዕከል፣ ቀበና፣ በአራት ኪሎ ፕላዛ (Underpass) ውስጥ የሚገኙ ሱቆችን እና ቦታዎች ለማከራየት
ሎት 2 :- ገዳመ ኢየሱስ ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደርለማከራየት፣
ሎት 3 ኮልፌ ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፣
ሎት 4 ፡ አምሳደር ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፣
ሎት 5 ፡-ሚሊንየም ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፣
ሎት 6 : መለስ ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፣
ሎት 7 ፡ አቃቂ ፓርክ ሙሉ ለሙሉ ለሶስተኛ ወፃን በማስተላለፍ እንዲተዳደር ለማከራየት፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የተጠቀሱትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ተጋብዘዋል፡፡
1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. ፓርኮቹ ውስጥ ገብቶ ለመስራት ፍቃደኛ የሆነና ከተቋማችን ጋር ውል ገብቶ በገበያ ጥናት እና የመነሻ ዋጋ መሰረት ተወዳድረው አስፈላጊውን ከፍያ የሚከፍልና በውሉ መሰረት ግዴታውን መወጣት የሚችል፡፡
3. በግቢ ያሉ ፋውንቴኖችንና ፣ መናፈሻዎችን ፣ የመጸዳጃ ቤቶችን ፣ የጽዳት ፣ የጥበቃ የተለያዩ ጥገናዎችን ከሌሎች ተከራዮች ጋር በመሆኑ ማስጠገን ፣ መቆጣጠርና በአግባቡ ማስተዳደርየሚችል፡፡
4. ለህዝብ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ተመጣጣኝ የገበያ ዋጋ ለማቅረብ ፍቃደኛ የሆነ፡፣
5. ኮርፖሬሽኑና የከተማ አስተዳደሩ በሚወጣው የሰራ ሰአት ፣ ቅዳሜ እና እሁድ ፣ በአላትን እንዲሁም ምሽትን ጭምሮ አገልግሎት መስጠት የሚችል፡፡
6. አሸናፊነት ከታወቀ በኃላና ውል ከወሰደ በኃላ በ3 ቀን ውስጥ ስራ መጀመር የሚችል፡፡
7. ስታንዳርዱን የጠበቀ እና የኮሪ ደር ልማቱን የሚመጥን እቃዎችን ይዞ መግባት የሚችል፡፡
8. ከተቻለ በሬስቶራንት ፤ በካፌ እና ህዝብ መዝናኛ ፓርክ ላይ ልምድ ያለውና መረጃ ማቅረብ የሚችል።
9. ተጫራቾች ለእያንዳዳቸው ሎቶች 50.000.00 (ሀምሳ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም ባንከ ጋራንቲ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደርኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
10. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ መገናኛ ዘፍመሽ ፊት ለፊት ታሜጋዝ ህንጻ ላይ ሶስተኛ ፎቅ የፋይናንስ ዳይሬክትሬት ቢሮ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር ተከታታይ የስራ ቀን ከጠዋት 2፡30 እስከ 11.30 ሰዓት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
11. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ዶክመንት እና ቴከኒካል ዶክመንት ለየብቻ በማሸማ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት ከoኛው ተከታታይ የስራ ቀን በኃላ በአለው ክኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
12. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ጠዋት 4፡30 መገናኛ ዘፍመሽ ፊት ለፊት ታሜጋዝ ህንጻ ላይ ሶስተኛ ፎቅ በግዥና ንብረት ዳይሬክትሬት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
13. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ሰኞ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
14. ዘግይቶ የደረሰ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
15.ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡-ስልክ ቁጥር 077619010 /0977246014 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች