አዲስ ዘመን የካቲት 05 ፣2016
Feb 20, 2024
11
Addis Ababa
Free
Check document for details
የግልፅ እና የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ዕቃ፣ ፅዳት፣ ልዩ ልዩ፣
ጫማ፣ ምግብ ነክ፤ የቤት ማስዋቢያ፣ አልባሳት፥ ኮንስትራክሽን እና እስፔርፓርት እቃዎች በሃራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች ከቀን 07/06/2016 ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች:-
1. ለግልፅ እና ለሀራጅ ጨረታ ለዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፥ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያው፤
2. ለሀራጅ ጨረታ ለመሳተፍ የተለያዩ እቃዎች ለመግዛት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 ሰ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማቅረብ የሚችል፤
3. ለግልታ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማቅረብ የሚችል፤
4. ለሃራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል፤
5. ለግልጽ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
6. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን የተለያዩ ዕቃዎች ወዲያውኑ ከፍሎ በ5 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት፤
7. እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ5 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
8. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙተት ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤
9. ማንኛውም ተጫራች የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ሲ.ፒ.አ (C.P.O) አሰርቶ ማምጣት አለበት፤
10. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
11. ማንኛውም ተጫራች የተለያዩ እቃዎች ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው እርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤
12. ተጫራቹ የተለያዩ እቃዎች አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፤
13.ተጫራቾች የሞሉትን የግልጽ ጨረታ ሰነድ 12/06/2016 ከጠዋት 2:00 እስከ 3:45 ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ ጨረታው 3፡45 ተዘግቶ በቀን 12/06/2016 ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤
14. የሀራጅ ጨረታው የሚካሄደው በቀን 12/06/2016 ከረፋዱ 4፡30 በቅ/ጽ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፣
N.B:- አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት