FREE TENDER | ነፃ ጨረታ
ቀጥሎ የቀረበው ጨረታ ክፍያ የማይጠይቅና አባል መሆን ሳይጠበቅብዎት የሚመለከቱት ነፃ ጨረታ ነው ሌሎች ሁሉንም ጨረታዎች ለማግኘት በዋልያ ቴንደር ደንበኛ አካውንትዎ እዚህ ይግቡ አባል ካልሆኑ እዚህ ይመዝገቡ
These tenders are free to view. You don't need to be a walia tender member to view them.
ጨረታ ማስታወቂያ
የምዕ/ሸዋ ማረሚያ ቤት ውስጥ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የበለጠ ምግብ አቅርቦት ከሐምሌ 01/2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ለአንድ ዓመት የሚቆይ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ማንኛውም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ፡-
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ወይንም ቢሮ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና አግባብነት ያለው የ2015 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው መሆኑ ይጠበቅባቸዋል።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ የተመዘገበ እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ፣
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30/ሠላሳ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከዞኑ ከአምቦ ማረሚያ ቤት ጽ/ቤት ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ/ በማድረግ በዞኑ አምቦ ማረሚያ ቤት ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2% በጥሬ ገንዘብ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /CPO/ እና
- በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ተደራጅተው የበሰለ ምግብ ለሚያቀርቡ ማህበራት ሁሉ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀን ቆይቶ በ16/አሥራ ስድስተኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ዕለት በ4፡30 ሰዓት በዞኑ አምቦ ማረሚያ ቤት ተጫራቾቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የሕግ ታራሚ ኮሚቴዎችና የመሥ/ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ይከፈታል። በ16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ የዞኑ አምቦ ማረሚያ ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን
የምዕራብ ሸዋ ዞን ማረሚያ ቤቶች ጽ/ቤት