አዲስ ዘመን የካቲት 02፤2018
Feb 24, 2026
15
Amhara
1000 ETB
በሎት ይለያያል
በድጋሚ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ለተፈጥሮ ሀብት መሬት አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት አገልግሎት የሚውል ሎት 01 የችግኝ ማፍያ ፕላስቲከ ባለ 10፣ ሎጎ 02 የእጅ ጋሪ እና ሎት 03 የውሃ ማጠጫ ጆርዲን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. በዘርፉ የተሰማሩ እና በዘመኑ ስለመታደሱ የሚገልጽ እና ግብር የከፈሉበትን ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከአርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የሚገዙ የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ጆርዲን እና የዕጅ ጋሪ ግዥ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00/አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ የዕቃ የግንባታ ወይም የእገልግሎት ዋጋ ብር በቁርጥ ዕለት 01 ብር200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እንዲሁም ለሎት 02 50,000.00/ሃምሳ ሺህ ብር/ ሎት 03 50.000.00/ሃምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) እና በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ( Unconditonal Bank Guarantee)ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ/የመወዳደሪያ/ ሃሳቡን የቴክኒካል ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው እና የፋይናሽያል ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪያውን በአንድ ዋና እና ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ጊቢ ቢሮ ቁጥር 025 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ለተጠየቁት ግዥዎች ናሙናቸውን ከቴከኒካል ሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 16ኛ ቀን ቅዳሜ ና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 2205849/0583208095/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
11. ተጫራቶች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ላይኖረው ይቻላል፡፡ ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት፡፡
12.በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ