የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና⁄ ኢኮ/ልማት መምሪያ የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስ/ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2016 በጀት ዓመት በታቀደው መሠረት በኮብልስቶን መንገድ ጥገና ከሎት HCA/Stat/CW-0017/2023/24 እስከ HCA/Stat/CW-0018/2023/24 ድረስ ያለው መንገድ ለሥራው በተዘጋጀው የስራ ዝርዝር መሠረት በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸው ማህበራት መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

Opens On: Jun 01, 2024
Closes On: Jun 01, 2024
Region: Sidama
Source: አዲስ ዘመን ግንቦት 3 ፣2016

ጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና⁄ ኢኮ/ልማት መምሪያ የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስ/ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2016 በጀት ዓመት በታቀደው መሠረት በኮብልስቶን መንገድ ጥገና ከሎት HCA/Stat/CW-0017/2023/24 እስከ HCA/Stat/CW-0018/2023/24 ድረስ ያለው መንገድ ለሥራው በተዘጋጀው የስራ ዝርዝር መሠረት በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸው ማህበራት መካከል በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማህበራት መወዳደር ይችላሉ።
1. በኮብልስቶን መንገድ ግንባታ ሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት፤-
2. በሥራ መስክ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፤
3. ተጨማሪ አሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፤
4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር ) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒአ (CPO ) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
6. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 (አስር) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል ሰነድ በመግዛት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ፡፡ 

7. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናት በፋይ/ኢኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 (ግዢ ኬዝ ቲም ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ጨረታው በ22ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 4፡00 ሠዓት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች በሲዳማ ክልል እና ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ተመሳሳይ ሥራ በእጁ ላይ ካለና የሥራው አፈጻጸም 70% ካልደረስ በጨረታ መወዳደር አይችልም፡፡ ሥራው 70% እና በላይ የደረሰ ከሆነ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማረጋጋጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
10. በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲከ ቼክ በሚደረግበት ግዜ በሁለቱ መካከል ከ2% (ከሁለት ፐርሰንት) በላይ ሆነ በታች ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
11. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ላይ ከ አሥራ አምስት ፐርሠንት (15%) በላይ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
12. ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበ የመሐንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ታች ከአሥራ አምስት ፐርሠንት (15%) በታች ከሆነ ለእያንዳንዱ ሥራ ዝርዝር ተጨባጭ የወቅቱ ገበያ የዋጋ ትንተና (Direct Unite cost Analysis sheet) ማቅረብ የሚችል እና ለዚህም መ/ቤቱ የጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ወይም መያዣ ገንዘብ መጠን ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል።
13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 046-220-99-63/046-212-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና /ኢኮ/ል/መምሪያ
ሀዋሳ


← Go Back

Advertisement


Put Your Ads Here, Reach More Peoples
& Business
call us +251942125616