Saved to Favorites!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ቦንኬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ሎት መሠረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Source | ምንጭ

አዲስ ዘመን ጥር 14 ፣2016

Closing | መጨረሻ

Feb 07, 2024

Views | እይታዎች

2

Region | ክልል

SNNPR

Doc Price

Free

CPO / Conditions | ሁኔታዎች

Check document for details

Description | ዝርዝር መግለጫ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በ2016 በጀት ዓመት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ቦንኬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ሎት መሠረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት
• ሎት አንድ፡-ጽህፈት መሳሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች -
• ሎት ሁለት፡- ኤሌከትሮኒክስ
* ሎት ሶስት -የተሸከርካሪ ጥገና አገልግሎት :

በግልጽ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ ፡፡
1ኛ/ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው/ያላት,
2ኛ/ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ TIN/ያለው
3ኛ/ ቫት /NAT/ ተመዝጋቢ የሆነ
4ኛ/ በበጀት ዓመቱ በሚወጣው ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች
የተሰጠ ከሊራንስ ወይም ድጋፍ ደብዳቤ ያለው
5ኛ/ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ
6ኛ/ ንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያለው
7ኛ/ ተጫራቾች የጨረታውን ሙሉ መረጃ ዝርዝር ከጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
8ኛ ፋይናንሻል ጨረታ ሰነዱ ዋጋ ተሞልቶ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶግራፊክ ኮፒ ሆኖ ኦርጅናሉ ለየብቻ ታሽጎ ከላዩ ላይ ፋይናንሻል ኦርጅናል ተብሎ መፃፍ አለበት፡፡ፎቶግራፊክ ኮፒው ለየብቻ ታሽጎ ፋይናንሻል ኮፒ ተብለው መፃፍ አለበት፡ቴክንካል ዶክመንት ለየብቻ መታሸግ አለበት
9ኛ/ ሁሉንም ፖስታዎች በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማድረግ በአግባቡ ታሽጎ ጨረታው በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት (ቅዳሜ፣ ዕሁድ እና በዓል ቀናትን ጨምረው) በሚቆጠር ሆኖ የጨረታውን ሰነድ መግዣ ለሎት አንድ የማይመለስ 200.00/ሁለት መቶ ብር/ እና ለሎት ሁለት የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር ) ለሎት ሶስት የማይመለስ 300.00(ሶስት መቶ ብር) በቦንኬ ወረዳ ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
10ኛ/ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ ወይም ዕሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ከቫት ጋር ዝቅተኛ ዋጋ ያስገባ ይሆናል፡፡
11ኛ/ ሎት ሶስት (የተሸከርካሪ ጥገና አገልግሎት) ያሸነፈው ተጫራች ውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 5% በማስያዝ ውል መግባት ይጠበቅበታል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ መሰረዝ ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ ዝርዝር መረጃ ከፈስጉ ስልክ ቁጥር +251916076775/+25 1913845574/251924745056
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ቦንኬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

PDF Export is locked for your plan.