Saved to Favorites!

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርምር፤ላቦራቶሪና ሥልጠና ማዕከል የኮንስትራክሽን ማቴሪያልና ጂኦቴክኒካል ላቦራቶሪ ምርመራ ተረፈ ምርቶችን የኮንክሪት፣የብሎኬት፣የአሸዋና ጠጠር፣የአፈር ወዘተ ተረፈ ምርት በየሳምንቱ ወይም በሁለት ሳምንት አንድ ቀን ጭኖ የሚያስወግድ በአንድ ቢያጆ 9M2 መጫን የሚችል ገልባጭ መኪና አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ማሰራት ይፈልጋል

Source | ምንጭ

አዲስ ዘመን ህዳር 14፣ 2016

Closing | መጨረሻ

Dec 05, 2023

Views | እይታዎች

10

Region | ክልል

Addis Ababa

Doc Price

Free

CPO / Conditions | ሁኔታዎች

Check document for details

Description | ዝርዝር መግለጫ

የጨረታ ማስታወቂያ 

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርምር፤ላቦራቶሪና ሥልጠና ማዕከል የኮንስትራክሽን ማቴሪያልና ጂኦቴክኒካል ላቦራቶሪ ምርመራ ተረፈ ምርቶችን የኮንክሪት፣የብሎኬት፣የአሸዋና ጠጠር፣የአፈር ወዘተ ተረፈ ምርት በየሳምንቱ ወይም በሁለት ሳምንት አንድ ቀን ጭኖ የሚያስወግድ በአንድ ቢያጆ 9M2 መጫን የሚችል ገልባጭ መኪና አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ማሰራት ይፈልጋል፡፡ 

በዚህም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት መወዳደር ይችላል፡፡ 

1. ተጫራቾቹ የ2016 ዓ.ም ፈቃድ ያደሰና ግብር የከፈለ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆኑን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤ 

2. ተጫራቾች በንግድ መስኩ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃዳቸውን፣ዓመታዊ የሥራ ግብር የከፈሉበትን፣በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታክስ NAT የተመዘገቡበትን የሚገልጽ መረጃ ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒውን ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡ 

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቹን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ጠዋት ከ2፡3-6፡30 ከሰዓ 7፡30-1፡00 የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር / በመክፈል በምርምር ላብራቶሪና ስልጠና ማዕከል ህንጻ የማዕከል ሀብት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ 

4. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በባንክ የተመሰከረለት ቼክ/CPO/ ከጨረታው ኦርጅናሉ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡ 

5. ማንኛውም ተጫራች እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ የጨረታ ዓይነቱ በግልጽ በመፃፍ ኮፒ እና ኦርጅናሉን በመለየት በምርምር፣ ላቦራቶሪና ሥልጠና ማዕከል ሀብት አዳደር ቢሮ ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡ በተጨማሪም ዋጋው ሲሞላ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም፡፡ 

6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምርምር፣ ላቦራቶሪና ሥልጠና ማዕከል ሀብት አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፡፡ 

7. የጨረታው አሸናፊ ማሽነፉ በፁሑፍ ከተገለፀለት ከ 7ኛ የሥራ ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡ 

8. ጨረታው የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ሳጥኑ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚህ ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከዋለ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል፡፡ 

9. ተረፈ ምርቱን የሚገኘው ቦታ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቅጥር ግቢ ውስጥ የቀድሞው ኢምፔሪያል ሆቴል ፊት ለፊት ወደ ስፖርት አካዳሚ በሚወስደው መንገድ እና በትራንስፖርት ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ዘርፍ ቅጥር ግቢ (ሜክሲኮ አከባቢ የኢትዮጲያ መንገዶች ባለስልጣን ጀርባ ወይም ቡናና ሻይ ባለስልጣን አጠገብ) ውስጥ በሚገኘው የማቴሪያል ላብራቶሪ ይሆናል፡፡ 

1o.አሸናፊው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊዎቹ ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል፡፡ 

ከመ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ 

አድራሻ ፡ የቀድሞው ኢምፔሪያል ሆቴል ፊት ለፊት ወደ ስፖርት አካዳሚ በሚወሰደው መንገድ 

ስልክ ቁጥር 011872591 እና on8721361 

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች 

ኮርፖሬሽን የምርምር፣ሳቦራቶሪና ሥልጠና ማዕከል _ 

 

PDF Export is locked for your plan.