አዲስ ዘመን ጥር 27 ፣2016
Feb 13, 2024
2
Addis Ababa
Free
Check document for details
በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች
25/2016
አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ከፍሎች፣ የኤሌክትሮንከስ ዕቃዎችን የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) ባሉበት ሁኔታ በግልፅና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑ እንገልጻለን፡፡ በመሆኑም፡-
1. በቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን በጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም CPO ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን ለሃራጅ ጨረታ ደግሞ ከጨረታ አንድ ቀን በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል፡፡
2. ተጫራቾች የግልፅና የሀራጅ ጨረታውን ሠነድ ከሀሙስ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
3. በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ፅ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMSSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE አዲስ አበባ በሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ብር 100,000.00 Sanct ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በተ.ቁ 3 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት፡፡
5. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡
| ተ.ቁ | የቅ/ጽ/ቤቱ ስም | የጨረታው አይነት | የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ | የጨረታው የመዝጊያ እና የመከፈቻ ቀንና ሰዓት |
| 1 | አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ ቤት | ሃራጅ | እስከ 4/06/2016 | 5/06/2016 4:00 ሰአት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡ |
| ግልፅ | እስከ 5/06/2016 | 6/06/2016 3:45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ |
6. የጨረታው መክፈቻ ቦታ ኢአ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸው⁄ ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
7. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
8. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል:፡
9. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
10. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር - አዲስ አበባ ቃሲት ጉምሩክ:- 011-470-85-03
አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀስበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያስበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ
አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት