Saved to Favorites!

ቋሚና አላቂ እቃዎች፣የደንብ ልብስና ጫማ፣ መጋረጃ፣ የፅደት እቃዎች የመኪና ዕቃና ጎማ ከሀገር ውስጥ ተጫራቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ በጨረታው ለመሳታፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች አሟልተው መገኛት ይኖርባቸዋል።

Source | ምንጭ

አዲስ ዘመን መስከረም 5/2019

Closing | መጨረሻ

Oct 06, 2026

Views | እይታዎች

94

Region | ክልል

Southwest

Doc Price

100 ETB

CPO / Conditions | ሁኔታዎች

5000

Description | ዝርዝር መግለጫ

የግልጽ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01 2019 ዓ.ም የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል እቃዎችን የ2019 በጀት ዓመት የአንደኛ ዙርከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡-
ቋሚና አላቂ እቃዎች፣የደንብ ልብስና ጫማ፣ መጋረጃ፣ የፅደት እቃዎች የመኪና ዕቃና ጎማ ከሀገር ውስጥ ተጫራቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ በጨረታው ለመሳታፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች አሟልተው መገኛት ይኖርባቸዋል።
1. በንግድ ዘርፍ ወይም በመስኩ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
2.. የመንግስት ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ወቅታዊ የሆነ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
4. የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
5. ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
6. ከላይ በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለጹ የንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ የኦርጅናሉን ይዘት በጠበቀ መልኩ በግልጽ የሚነበብ መሆን አለበት።
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 አምስት ሺህ) ብር ሕጋዊ ከሆነ ባንክ የተረገጋጠ (CPO) በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ስም አሰርተው ከሚያቀርባቸው ሠነዶች ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው። ይህ እንዳላ ሆኖ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ አስቀድሞ ከባንከ ማረጋገጫ የሚወሰድ ይሆናል።
8. ማንኛውም ተጫራች በተራ ቁጥር 7 ላይ የተጠቀሰውን (CPO) ካላቀረበ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
9. ለጥቃቅን ኢንተርፕረይዞች ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ፋንታ ከአደራጁ መ/ቤት የተጻፈ ወቅታዊ የሆነ ሕጋዊ የድጋፊ ደብዳቤ መቅረብ ይኖርበታል።
10. ተጫራቶች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዶክመንት ወይም የጨረታው ሰነድ ከደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድቤት ወሊሶ ከተማ ቢሮ ቁጥር 12 ድረስ በአካል በመቅረብ የዕቃውን ምድብ አይነት /lot/ የማይመለስ 100/አንድ መቶ ብር/ ይህ ማስታወቂያ በዚህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ05/01/2019-እስከ 25/01/2019 ዓ.ም መግዛት ይችላሉ።
11. ጨረታውን ለማሰናከል የሚሞክር ተጫራች ከጨረታው ውጪ ሆኖ ወደፊት በሚደረገው በማንኛውም ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፤ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብም ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
12. የጨረታው ሰነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ የሚቆይ ይሆናል።
13. የጨረታው ሰነድ በ 26/01/2019 ከጠዋቱ እስከ 4:00 ድረስ ለጨረታ በተዘጋጀለት የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው የሚከፈተው በዚህ እለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።
14. መስሪያ ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆና በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
15. ከለይ በተራ ቁጥር 1-14 ሳያሟላ የሚቀረብ ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይሆናል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
አድራሻ፡-የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ወሊሶ ከተማ
ስልክ ቁጥር፡- 0113411484/0113411396
Email:-mmosk@oromiyaa.gov.et
የደቡብ ምዕ/ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት

PDF Export is locked for your plan.