መግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጨረታ እንዴት መሳተፍ እችላለሁ?
ኢትዮጵያ እንደ ተመድ፣ የአፍሪካ ኅብረት፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ወዘተ ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የዲፕሎማሲ ልዑካን ና፣ እንደ GIZ፣ MSF፣ Save the Children፣ ወዘተ ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መገኛ ናት፡፡ እነዚህ ድርጅቶች የየራሳቸውን ዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ጨረታ ወይም የፍላጎት መግለጫ (Expression of Interest) ማስታወቂያዎችን ያወጣሉ፡፡walia tender እነኚህን ዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ጨረታ ወይም የፍላጎት መግለጫ (Expression of Interest) ማስታወቂያዎችን ከነኚህ ድርጅቶች በመቀበል፣ ከተለያዩ ሀገር አቀፍ እና ክልላዊ ጋዜጦች በመውሰድ፣ ወዘተ ድረ ገጹ ላይ ለተጠቃሚ እንዲመች አድርጎ ይለጥፋል፡፡ እንግዲህ እነዚህን ማስታወቂያዎችን የሚያወጡ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የሚኖራቸው መስፈርት ከመንግሥት ድርጅቶች ቢለይም መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን ማሟላት ደግሞ የተሳታፊው (vendor) ድርሻ ይሆናል፡፡ እነዚህን መሰረታዊ የሚባሉትን ነገሮች ከዚህ በታች ይገኛሉ፡፡
የተሳታፊ (vendor) ምዝገባ
በመጀመሪያ ተሳታፊው ከተመድ (UN) ድርጅቶች ጋር መስራት ካስፈለገው በ http://www.ungm.org/ መመዝገብ ይኖርበታል። ሌሎች ድርጅቶችም የየራሳቸው የምዝገባ ዘዴ ወይም መስፈርት ይኖራቸዋል፤ ስለዚህም ተሳታፊው የየተቋማቱን የግዥ ክፍል በማነጋገር መመዝገብ ይገባዋል ምክንያቱም ተቋማት ወይንም ድርጅቶቹ በማስታወቂያዎች ሳያስነግሩ የተለያዩ አቅራቢዎችን(vendors) በቀጥታ ሊያነጋግሩ ስለሚችሉ ነው።
አስፈላጊ ሰነዶች
አስፈላጊ መረጃዎች (የግድ መሟላት ያለባቸው መረጃዎች):-
የታደሰ የንግድ ፈቃድ
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት
የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት (በአንዳንድ የንግድ ዘርፎች የተመዘገቡ ተሳታፊዎች ላያስፈልጋቸው ይችላል ፤ ለምሳሌ የፋርማሲውቲካልስ ቢዝነስ)
በተጨማሪ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መረጃዎች ተካተው ቢገኙ የተሻለ ይሆናል:-
የድጋፍ ደብዳቤ
የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት
የአገልግሎታችንን ጥራት ሊመሰክሩ የሚችሉ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ዝርዝር
አቀራረብ እና ኮሚውኒኬሽን
ጨረታ ወይም የፍላጎት መግለጫ (Expression of Interest) በሚሳተፉበት ጊዜም ሆነ ከዚያን ጊዜ ውጭ በሚኖርዎት ግንኙነት ራስዎንና ድርጅትዎን በሚገባና በጥሩ አቀራረብ ማሳየት መቻል አለብዎት፡፡
የፋክስ ወይም ደብዳቤ መልዕክት:- የድርጅትዎን ዓርማ እና አድራሻ በያዘ ወረቀት ላይ መጻፍ ይኖርበታል፡፡ ከመላክዎ በፊት መልዕክቱ ፊርማ እና ማህተም ማካተቱን እርግጠኛ ይሁኑ።
የኢሜይል መልዕክት:- የኢሜይል መልዕክት በሚልኩበት ጊዚ መልዕክቱ ጥራት ባለው መንገድ የተዘጋጀ የኢሜይል ፊርማ (ከዚህ በታች ማየት ይችላሉ)የያዘ መሆን አለበት። ኢሜይሉ ጋር ተያያዥ የሆኑ የፋክስ ወይም ደብዳቤ መልዕክቶች ካሉም መልዕክቶቹ የድርጅትዎን ዓርማ እና አድራሻ በያዘ ወረቀት ላይ መጻፍና ፊርማ እና ማህተም ማካተት ይኖርባቸዋል፡፡
የኢሜል ፊርማ ሊያካትታቸዉ የሚገቡ ነገሮች:- የተሳታፊዉ ስም፣ የስራ ኃላፊነት፣የድርጅት ስም እና አድራሻ፣ስልክ (የቢሮ እና የግል ወይም ሞባይል)፣ፋክስ እና የኢሜል አድራሻ እና የድርጅት ድረ ገጽ (ካለ)
ፕሮፌሽናል የሆነ የኢሜይል አድራሻ:- የኢሜይል አድራሻዎ በድርጅትዎን ድረ ገጽ በኩል ከሆነ ወይንም የእርስዎ ሙሉ ስም ወይንም የድርጅትዎ ሙሉ ስም የያዘ ከሆነ ድርጅትዎ ፕሮፌሽናል የሆነ የኢሜይል አድራሻ አለው ማለት ነው፡፡
ሌሎች የኢሜይል አድራሻዎችን በራስዎ ወይም በድርጅትዎ ስም መፈጠር የሚችሉ ሲሆን የኩባንያዎን ስም የያዘ የስራ ስም ካለዎት Gmail መጠቀም ይችላሉ፡፡ Gmailን መጠቀም በኢንዱስትሪ ዉስጥ Yahooን ከመጠቀም ይልቅ ለባለ ድርጅቶች የተሻለ ፕሮፌሽናል እንደሆነ ይታወቃል፡፡ Gmail በሚጠቀሙበት ጊዜ ስምዎን (የድርጅትዎን ሊሆን ይችላል) እንደ ኢሜይል ID መጠቀም ይኖርበዎታል:- ለምሳሌ
ትክክለኛ የእንግሊዝኛ ቋንቋ አጠቃቀም:- ዓለም አቀፋዊ ከሆኑ ተቋማት ጋር መልዕክት በሚለዋወጡበት ጊዜ አግባብ ያለዉን እንግሊዝኛ መጠቀም አለብዎት። በተጨማሪም በሚጻጻፉበት ወቅት በተቻለ መጠን የፊደል እና ሰዋሰዋዊ ግድፈቶችን (spelling and grammar errors) ማስወገድ ይኖርብዎታል፡፡