ውስን ጨረታ ምንድን ነው?

Source:walia tender May 22,2023

ውስን ጨረታ
የውስን ጨረታ ሥርዓቶች ከግልጽ ጨረታ ጋር ተመሳሳይ ሲሆኑ፣ የውስን ጨረታ የሚከተሉትን ልዩ አሠራሮች ይከተላል፡፡
፩. የጨረታ ጥሪው በጨረተው ለመሳተፍ ፍላጐት ላላቸው የተወሰኑ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ብዛት ውጤታማ የሆነ ውድድር እንዲኖር ለማድረግ የሚያስችል መሆን አለበት፡፡
፪. ግዥ ፈፃሚ አካላት በውስን ጨረታ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ የሚደረግላቸው ዕጩ ተወዳዳሪዎች የሚመርጡት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ከተመዘገቡት መካከል ይሆናል፡፡ አመራረጡ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለተመዘገቡ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ፍትሀዊ የሆነ ዕድል የሚያስገኝ መሆን ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በላይ የተነገረው ቢኖርም ዕጩ ተወዳዳሪዎች ጥሪ ቢደረግላቸው በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ መሆኑን መግለጽ እንዲችሉ ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፴፩/፩/ በተደነገገው መሠረት ማስታወቂያ ለማውጣት ይችላል፡፡
፫. ለጨረታው ሰነድ ዝግጅት የሚፈቀደው ጊዜ በግዥ መመሪያው ከተወሰነው አነስተኛ የቀን ብዛት ያነሰ ሊኝ አይችልም፡፡
፬. ግዥ ፈፃሚው አካል የግዥውን ሁኔታ መሠረት በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ የሚያስፈልግ መሆን ያለመሆኑን ይወሰናል፡፡


← Go Back

Advertisement


Put Your Ads Here, Reach More Peoples
& Business
call us +251942125616