፴፩. የጨረታ ማስታወቂያ
፩. የጨረታ ማስታወቂያ አገራዊ ሽፋን ባለው ቢያንስ አንድ ጋዜጣ ላይ መውጣት አለበት፡፡
፪. በዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማቅረቢያ የሚሰጠው ጊዜ በግዥ መመሪያ ከሚወሰነው አነስተኛ የቀን ብዛት ያነሰ መሆን የለበትም፡፡
፩. የግዥ ፈፃሚውን አካል ስምና አድራሻ፤
፪. ዕቃው መቅረብ ወይም ሥራው መጠናቀቅ ያለባቸውን ቅድመ-ሁኔታዎች እና የጨረታ ሰነዱ የሚገኝበትን ቦታ፣
፫. የጨረታውን ሰነድ ለማግኘት መሟላት ያላባቸውን ቅድመ-ሁኔታዎች እና የጨረታ ሰነዱ የሚገኝበት ቦታ፤
፬. የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳብ የሚቀርብበት ቦታ እና የማቅረቢያው የመጨረሻ ጊዜ፤
፭. ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ እና ጊዜ እንዲሁም ተጫራቾች ወይም ተወካዮች ጨረታው ሲከፈት መገኘት የሚተሉ መሆኑን የሚገልጽ ማሳሰቢያ፤
፩. በተጫራቾች መካከል የደረገው ውድድር በተሟላ፤ ገለልተኛና ተጨባጭ መሠረት ባለው ሁኔታ እንዲካሃድ ለማድረግ የጨረታው ሰነድ በቂ መረጃ የያዘ መሆን አለበት፡፡ በተለይም ሰነዱ የሚከተሉትን ሊያካትት ይገባል፡፡
ሀ. የጨረታ ሰነዱን ለማዘጋጀትና ለማቅረብ አስፈላጊ የሆኑ መመሪያዎችን፤
ለ. የጨረታ ሰነዱን ማስረከቡያ የመጨረሻ ቀን፣ የጨረታ ሰነዱ የሚላክበትን አድራሻ፤ የጨረታው ሰነድ የሚከፈልበትን ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ፣ እንዲሁም የተጫራቾች ወኪሎች በጨረተው መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ሊገኙ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ መረጃ፤
ሐ. የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳብ ማቅረቢያ ቅጾች፤ እንዲሁም አግባብነት እስካለው ድረስ የጨረተ ማስከበሪያ ቅጾች፤
መ. ከዋናው የጨረታ ሰነድ ጋር መቅረብ ያለባቸውን ተጨማሪ ኮፒዎች፤
ሠ. የውሉን አጠቃላይ እና ልዩ ሁኔታዎች፤
ረ. እንደአግባብነቱ ዕቃውን ለማቅረብ ወይም ሥራውነ ለማጠናቀቅ ይወስዳል ተብሎ የሚገመተውን የጊዜ ገደብ ጨምሮ ተፈላጊውን የዕቃና አገልግሎት ዝርዝር፤
ሰ. ተጫራቹ በጨረታው ለመሳተፍ ብቃት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያቀርባቸውን መረጃዎች ዓይነት እንዲሁም የፋይናንስ አቋሙን እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ መሆኑን ለማረጋገጥ ማቅረብ ያለበትን መረጃ፤
ሸ. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበትን ጊዜ፤
ቀ. ጨረታውን ለመገምገም እና በጨረታው አሸናፊ የሆነውን ለማስታወቅ የሚያገለግሉ መስፈርቶችን እና ለእያንዳንዱ መስፈርት የተሰጠውን ነጥብ፤
በ. ግዥውን የሚፈፅመው አካል የጨረታው አሸናፊ ይፋ ከመደረጉ በፊት በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን የመሠረዝ መብት ያለው መሆኑን፤
የጨረታ ሰነዶች ለጨረታው ሰነድ ዝግጅት እና ሰነዱን ለዕጩ ተወዳዳሪዎች ለማቅረብ ከወጣው ወጪ ባልበለጠ ዋጋ፣ በተፋጠነ ሁኔታ እና በጨረታ ማስታወቂያው በተገለፀው አኳኋን ለዕጩ ተወዳዳሪዎች እንዲደርሱ መደረግ አለበት፡፡
፴፭. በጨረታ ሰነድ ላይ ስለሚደረግ ማሻሻያ
፩. ግዥ ፈፃሚ አካላት በራሳቸው ወይም የጨረታ ሰነድ ከገዙ ዕጩ ተወዳዳሪዎች በሚቀርቡ ጥያቄዎች መነሻ የጨረታ ሰነዱ ማቅረቢያ ጊዜ ገደብ ከማለፉ በፊት የጨረታ ሰነዶችን ይዘት ለማሻሻል ይችላሉ፡፡
፪. የተደረገው ማሻሻያ በጽሑፍ ተዘጋጅቶ የጨረታ ሰነዶችን ለገዙ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ሁሉ በተገቢው ሁኔተ በእኩል እንዲደርስ መደረግ አለበት፡፡
፫. ግዥ ፈፃሚው አካል የጨረታ ሰነዱን ይዘት ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ያገኘው እና በማሻሻያው የተመለከቱ ማስተካከያዎችን ለማድረግ በቂ ጊዜ የሌለ መሆኑን የተረዳ እንደሆነ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ማሻሻያውን መሠረት አድርገው የጨረታ ሰነዱን ለማዘጋጀት በቂ ጊዜ እንዲኖራቸው ለማድረግ የግዥውን ባሕርይ መሠረት በድረግ የጨረታውን ማቅረቢያ ጊዜ ለተወሰኑ ቀናት ሊያራዝም ይችላል፡፡
፩. በዚህ አዋጅ በተለይ ካልተወሰነ በስተቀር ግዥ ፈፃሚ አካላት በሚያዘጋጁት የጨረታ ሰነድ ተጫራቾች ከጨረተ ሰነዶቻቸው ጋር በተቀማጭ ገንዘብ ወይም በጨረታ ዋስትና መልክ የጨረታ ማስከበሪያ የማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው መግለጽ አለባቸው፡፡ የጨረተ ማስከበሪያ መጠን በጨረታው ኃላፊነት በተሞላው ሁኔታ የማይሳተፉትን ለማሰቀረት የሚያስችል ሆኖ፣ በግዥ መመሪያው ከተወሰነው መጠን ያልበለጠ መሆን አለበት፡፡
፪. የጨረታ ማስከበሪያው ፀንቶ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ተጫራቹ ራሱን ከውድድሩ ካገለለ ወይም አሸናፊውን ተጫራች በሚመለከት አሸናፊነቱ የተገለፀለት ብኋላ ሙሉን ለመፈረም ፈቀደኛ ሆኖ ካልተገኘ ወይም እንዲያቀርብ የተጠየቀውን የውል ማስከበሪያ ካላቀረበ የጨረታ ማስከበሪያው ውርስ ይደረጋል፡፡
፩. የጨረታ ሰነድ በጽሑፍ ተዘጋጅቶና ተፈርሞበት በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ ሆኖ በጨረታ ማሰታወቁያው ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት በተገለፀው ቦታ ገቢ መደረግ አለበት፡፡
፪. የጨረታ ሰነድ ትልቅ በመሆኑ በጨረተ ሳጥን ውስጥ ሊቀመጥ የማይችል ከሆነ ግዥ ፈፃሚው አካል የጨረታ ሰነዱ ገቢ የተደረገበት ቀነና ሰዓት የሚያሳይ ደረሰኝ ለተጫራቹ መስጠት አለበት፡፡
፫. ከዚህ በላይ በንዑስ አንቀጽ ፪ የተገለጸው ዓይነት የጨረታ ሰነድ ለጨረታ ማቅረቢያ ከተወሰነው ጊዜ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ መመለስ አለበት፡፡
፩. ግዥ ፈፃሚው አካል በጨረታ ሰነዱ የተመለከተው ለጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ የተወሰነው የጊዜ ገደብ እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ፣ የጨረታ ሰነድ ከማቅረቢያ የጊዜ ገደብ በፊት የተረከባቸውን የጨረታ ሰነዶች መክፈት አለበት፡፡
፪. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ ሰነድ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንዲገኙ መጋበዝ አለባቸው፡፡
፫. የተጫራቹ ስም እና በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የቀረበው የመጫረቻ ዋጋ ድምር ከፍ ባለ ድምጽ መነበብ እና መመዝገብ እንዲሁም ተጫራቾች በጠየቁ ጊዜ የተመዘገበውን ዝርዝር እንዲያገኙ መደረግ አለበት፡፡
፩. ጨረታውን ለመመርመረና ግምገማውን ለማከናወን የሚረዳ ሆኖ ሲገኝ፣ ግዥ ፈፃሚው አካል ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ሆኖም የዋጋ ለውጥን ጨምሮ በጨረታው ሰነድ ላይ መሠረታዊ ለውጥ የሚያስከትል ሀሳብ ማቅረብ ወይም መፍቀድ አይቻልም፡፡
፪. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ የተመለከተው ቢኖርም ግዥ ፈፃሚው አካል በጨረታ ምርመራው ወቀት የተገኙ የሂሳብ ስህተቶችን ለማረም ይችላል፡፡ ግዥ ፈፃሚው አካል እነዚህን ማስተካከያዎች የጨረታ ሰነዱን ላቀረበው ተጫራች በአፋጣኝ መግለጽ አለበት፡፡
፫. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፬ የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ግዥ ፈፃሚው አካል ጨረታው የተሟላ ነው ብሎ ሊቀጥል የሚችለው በጨረታው ሰነድ የተመለከቱትን ተፈላጊ ሁኔታዎች ሙሉ በሙሉ የሚያሟላ ሆኖ ሲያገኘው ነው፡፡
፬. በጨረታው ሰነድ የተዘረዘሩት ባህሪያት፣ የውል ቃሎች፣ ሁኔታዎች እና ሌሎችም ተፈላጊ ነጥብ ጋር በተወሰነ ደረጃ ልዩነት ቢኖረውም መሠረታዊ የሆነ ለውጥ እና ልዩነት እስከሌለው ድረስ ወየም የጨረታው ቁምነገር ሳይለወጥ ሊታረም የማችል ጥቃቅን ስህተት ወይም ግድፈት ቢኖረውም ግዥ ፈፃሚው አካል ጨረተውን እንደተሟላ አድርጐ ሊቀበል ይችላል፡፡ ማናቸውም ልዩነት አስከተቻለ ድረስ በአሀዝ ተገልጾ በጨረታ ግምገማ እና ወድድር ወቅት ከግምት ውስጥ መግባት አለት፡፡
፭. ማናቸውም ግዥ ፈፃሚው አካል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የማያሟሉ ጨረታዎችን ለውድድር ማቀረብ የለበትም፡፡
ሀ. ተጫራቹ በአንቀጽ ፴፫ /ሰ/ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት የማይችል ሆኖ ሲገኝ፤
ለ. ተጫራቹ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ መሠረት የተደረገውን የሂሣብ ማስተካከያ የማይቀበል ሆኖ ሲገኝ፤
ሐ. የቀረበው የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳብ ተፈላጊውን የማያሟላ ሆኖ ሲገኝ፤
፮. ግዥ ፈፃሚው አካል በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፯ በተደነገገው መሠረት አሸናፊውን ተጫራች ለመምረጥ በጨረታ ሰነዱ በተመለከተው ሥርዓት እና የግምገማ መስፈርት መሠረት ተፈላጊውን የሟሉ የጨረታ ሰነዶችን መገምገምና ማወዳደር አለበት፡፡ በጨረታ ሰነድ ያልተመለከተ የማወዳዳሪያ መስፈርት በጥቅም ላይ ሊውል አይችልም፡፡
፯. በጨረታ አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው፤
ሀ. በጨረታ ገምገማ የቴክኒክ መመዘኛዎችን ማማላቱ የተረጋገጠ እና አነስተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች፤ ወይም
ለ. ግዥ ፈፃሚው አካል በጨረታው ሰነድ ውስጥ አሸናፊው ተጫራች የሚመረጥበትን መስፈርት የገለፀ ከሆነ፤ በጨረታ ሰነዱ የሰፈረውን የጨረታውን ኢኮኖሚያዊ እሴት የሚወስነው መስፈርት መሠረት በማድረግ በሚካሄድ ግምገማ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች አሸናፊ ይሆናል፡፡ ሆኖም መስፈርቱ በተጨባጭ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ፣ በአኃዝ ሊገለጽ የሚችል ሆኑ በግምገማው ሂደት አንፃራዊ ክብደት የሚሰጠው እና እስከተቻለ ድረስ በገንዘብ የሚገለጽ መሆን አለበት፡፡
፰. ግዥ ፈፃሚው አካል የጨረታ ሰነድ ምርመራና ግምገማውን ውጤት በአጭሩ የሚገልጽ የግምገማ ሪፖርት ማዘጋጀት አለበት፡፡
፵. በሚስጥር ስለሚያዙ አሠራሮች
፩. ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ አንስቶ ከጨረታ ምርመራ፣ ከማብራሪያ ከግምገማ እና አሸናፊውን ተጫራች በሚመለከት ከቀረበው የውሣኔ ሃሳብ ጋር የተያያዙ መረጃዎች በሚስጢርነት መጠበቅ ያለባቸው ሲሆን፤ አሽናፊው ተጫራች እስከሚገለጽ ድረስ ለተጫራቾች ወይም ከሥራው ሂደት ጋር ግንኙነት ለሌላቸው ሰዎች መገለጽ የለባቸውም
፪. ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ አንስቶ ውሉ እሰከሚፈረም ድረስ ማናቸውም ተጫራች በማናቸውም አኳኋን የጨረታውን ምርመራና ግምገማ ለማዛባት መሞከር የለበትም፡፡
፫. ጨረታው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ውሉ እስከሚፈረም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ዕጩ ተወዳዳሪው ከጨረታው ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ከግዥ ፈፃሚው አካል ጋር ግንኙነት ማድረግ የሚችለው በጽሑፍ ብቻ ይሆናል፡፡
፵፩. በጨረታው አሸናፊ እንዲሆኑ ለማድረግ ተጫራቾች ያቀረቡትን የመወዳዳሪያ ሀሳብ አሻሽለው እንዲያቀርቡ በቅድመ-ሁኔታነት መጠየቅ የማይቻል ስለመሆኑ ማናቸውም ተጫራች በጨረታው ሰነድ ከተመለከተው ውጪ፤ በጨረታው አሸናፊ ለመሆን ያቀረበውን የመጫረት ዋጋ እንዲለወጥ ወይም በሌላ አኳኋን ያቀረበውን መወዳደሪያ ሀሳብ እንዲያሻሽል ወይም ይህንን ለመፈፀም ግዴታ እንዲገባ በቅድመ-ሁኔታነት ሊጠየቅ ወይም ሊገደድ አይችልም፡፡
፩. ግዥ ፈፃሚ አካላት የመወዳደሪያ ሀሳቡ ፀንቶ የሚቆይበት ቀን ከማለፉ በፊት በጨረታው አሸናፊ ለሆነው ተጫራች አሸናፊነቱን መግለጽ አለባቸው፡፡ የአሸናፊነት መግለጫ ማስታወቂያው ውሉ የሚፈረመበትን ጊዜ የሚገልጽ ይሆናል፡፡ በጨረታው ተሸናፊ ለሆኑ ተጫራቾችም የአሸፊውን ስም እና የተሸነፉበትን ምክንያት የሚገልጽ ማስታወቂያ ሊደርሳቸው ይገባል፡፡
፪. በግዥ ፈፃሚው አካል እና በአቀራቢው መካከል ውል ተመስርቷል የሚባለው በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች ስምምነት የተደረሰባቸውን ጉዳዮች በሙሉ የሚይዘው የውል ሰነድ ሲፈረም ይሆናል፡፡
፫. ግዥ ፈፃሚው አካል ለተሸናፊዎቹ ተጫራቾች ተሽናፊነታቸውን የሚገልፀው ማስታወቂያው ከመድረሱ እና በአንቀጽ ፶፪ የተመለከተው የጊዜ ገደብ ከማለፉ በፊት የግዥውን ውል መፈረም የለበትም፡፡
፵፫. የውል ማስከበሪያ አቅራቢው በውሉ መሠረት ባለመፈፀሙ በግዥ ፈፃሚው አካል ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ማካካሻ የሚውል የውል ማስከበሪያ ለግዥ ፈፃሚው አካል መስጠት አለበት፡፡ የውል ማስከበሪያ የሚጠየቅባቸው የግዥ ዓይነቶች፣ የውል ማስከበሪያው ዓይነትና መጠን ሚኒስትሩ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡